Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በጥምቀት በዓል ላይ ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በጥምቀት በዓል ላይ ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከጥር እስከ ጥር ታሪክ፣ ባህል ትውፊትና እምነት ከሚነገርባት እና ከሚዘመርባት ሙዝየሟ ከተማ ጎንደር ገብተናል ብለዋል።

በከተማዋ በሚኖራቸው ቆይታ፣ ታሪካዊ ሥፍራዎችን እና ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ጠቁመዋል።

ከፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ጋር በመሆን ጎንደር ዐፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ለተደረገላቸው የሞቀ አቀባበል አመስግነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.