በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዛሬ 9 ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
5 ሰዓት ማርሴ ከሊቨርፑል፣ ስላቪያ ፕራግ ከባርሴሎና፣ ባየር ሙኒክ ከሮያል ዩኒየን እንዲሁም ቼልሲ ከፓፎስ ይጫወታሉ።
በተመሳሳይ ሰዓት አትላንታ ከአትሌቲክ ቢልባኦ፣ ጁቬንቱስ ከቤኔፊካ እንዲሁም ኒውካስል ከፒኤስቪ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የጣሊያንኑ ክለብ ጁቬንቱስ ከወራጅ ቀጠና ለመራቅ ጠንካራ ፍልሚያ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪ ቀደም ብሎ ምሽት 2 ሰዓት ላይ ጋላታሳራይ ከአትሌቲኮ ማድሪድ እንዲሁም ካራበርግ ከፍራንክፈርት ይፋለማሉ።
ትናንት በተደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች አርሰናል ኢንተር ሚላንን 3 ለ 1፣ ሪያል ማድሪድ ሞናኮን 6 ለ 1፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ፒኤስጂን 2 ለ 1፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ቦሩሺያ ዶርትመንድን 2 ለ 0፣ እንዲሁም ኦሎምፒያኮስ ባየር ሊቨርኩሰንን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
አያክስ አምስተርዳም ከሜዳው ውጪ ቪያሪያልን 2 ለ 1፣ ቦዶ ግሊምት ማንቼስተር ሲቲን 3 ለ 1፣ ክለብ ብሩጅ ካይራት አልማቲን 4 ለ 1 ሲያሸንፉ፤ ኮፐንሀገን እና ናፖሊ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወቃል፡፡