Fana: At a Speed of Life!

ካፍ በአልጄሪያ ላይ የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በአልጄሪያ ላይ የ100 ሺህ አሜሪካን ዶላር ቅጣት አስተላልፏል።

ቅጣቱ የተላለፈው አልጄሪያ እና ናይጄሪያ ባደረጉት የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የአልጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጨዋቾችና ደጋፊዎቻቸው ተገቢነት የሌለውን ባሕሪ በማሳየታቸው እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም ግብ ጠባቂው ሉካ ዚዳን ሁለት ጨዋታዎችን ሲታገድ÷ ተከላካዩ ራፊክ ቤልጋሊ ከአራት ጨዋታዎች እንዲታገድ ተወስኖበታል።

ቅጣቶቹ በፈረንጆቹ 2027 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ወቅት ተግባራዊ እንደሚገደረግም ተመላክቷል።

በተጨማሪም ደጋፊዎች ተቀጣጣይ ነገሮችን በመጠቀም፣ ቁሳቁስ በመወርወር እና የዳኝነት ቡድኑ ላይ የጥቃት ምልክቶች በማሳየታቸው ምክንያት በአልጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ላይ የ100 ሺህ አሜሪካን ዶላር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።

የአልጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን በመቃወም የይግባኝ ሂደት መጀመሩንና በህጋዊ መንገዶች እንደሚከላከል ማሳወቁን ፉትቦል ዋን ዘግቧል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.