Fana: At a Speed of Life!

ከወጪ ንግድ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባለፉት 6 ወራት ከወጪ ንግድ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል አሉ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የ6 ወራት የንግድ ዘርፍ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ ባለፉት 6 ወራት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 42 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ከ5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።

በዚህም የእቅዱን 120 በመቶ መፈጸም መቻሉን ጠቅሰው ÷ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ1 ነጥብ 83 ቢሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።

ለኢትዮጵያ ማንሠራራትና ለተቋም ግንባታ መሰረት የጣሉ ስኬቶችን አስመዝግበናል ያሉት ሚኒስትሩ÷ በንግዱ ዘርፍ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሁለት ሚሊየን በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦንላይን መሰጠቱን ነው የገለጹት፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከወጪ ንግድ 9 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል።

በከድር መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.