Fana: At a Speed of Life!

ካሴሚሮ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ይለያያል

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ33 ዓመቱ ብራዚላዊ አማካይ ካሴሚሮ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚለያይ ተነግሯል።
ተጫዋቹ በዩናይትድ የሚያቆየው ውል በመጪው ክረምት ሲጠናቀቅ ለተጨማሪ አንድ አመት ቆይታውን የማራዘም አማራጭ ቢኖርም ክለቡ ውሉን ለማራዘም ፍላጎት እንደሌለው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ይህን ተከትሎ የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ኮከብ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚለያይ ተገልጿል።
ተጫዋቹ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፥ በኦልድትራፎርድ የነበረው ቆይታ ከአራት ወራት በኋላ እንደሚያበቃ አረጋግጧል።
ተጫዋቹ በእስካሁን የዩናይትድ ቤት ቆይታው 146 ጨዋታዎችን በማድረግ 21 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
4ኛ የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር እያሳለፈ የሚገኘው ካሴሚሮ አንድ የኤፍ ኤ እና አንድ የካራባኦ ዋንጫን አሳክቷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.