Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ስድስት ወራት ከ377 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት መሳብ ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ2018 ግማሽ በጀት ዓመት ከ377 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል አለ።

በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በለጠ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት ከ377 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ 64 ባለሃብቶች ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመሳብ ተችሏል፡፡

ንግድና ሎጂስቲክስ፣ ፋርማሲዩቲካል፣ አግሮ ፐሮሰሲንግ፣ ኢንጂነሪንግና ብረታ ብረት፣ ኮንስትራክሽንና ፈርኒቸር እንዲሁም አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ ባለሃብቶቹ የተሰማሩባቸው የስራ ዘርፎች መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ከተሰማሩ ባለሃብቶች መካከልም ከቻይና፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ህንድ እና ጅቡቲ የመጡ መኖራቸውን ጠቁመዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው በመስራት ላይ በሚገኙ ባለሃብቶች ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ112 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱም ተመላክቷል፡፡

በአድማሱ አራጋው

👉ለፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች የፋና ዲጂታል አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ፡-

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.