Fana: At a Speed of Life!

እየተጠናከረ የመጣው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ትብብር…

እየተጠናከረ የመጣው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ትብብር...

አዲስ አበባ፣ ጥር ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች እና የአፍሪካ ህብረት ያላቸው ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ እየተጠናከረ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሚኒስትር ዴዔታ የሆኑት ሼክ ሻክህቦት ቢን ናህያን አል ናህያን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም እስካሁን በተካሄዱ ምክክሮች የተመዘገበው ውጤትና  እድገት የተገመገመ ሲሆን÷ ሁለቱ ወገኖች ለትብብር ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

በተጨማሪም በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ቀጣይነት ያለው ውይይትና ትብብር ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱም ወገኖች በ2030 የጦር መሳሪያ ድምጽ የማይሰማበት ቀጣና ለመፍጠር የተያዘውን አቅድ ለማሳካትና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናን ለማጠናከር በቅንጅት እንደሚሰሩ አመልክተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በሰላም፣ ደህንነት፣ ንግድ እና ልማት ያላቸው ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡

ዘላቂ ሰላም ለኢኮኖሚ ውህደት መሠረት መሆኑን በመገንዘብ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት መጨመር በአፍሪካ መረጋጋት፣ የመቋቋም አቅም እና ዘላቂ ልማት ላይ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተጠቁሟል።

እነዚህን ስትራቴጂካዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለመደገፍ ትብብርን ለማሳደግ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተመላክቷል፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታን ለማሳደግ “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለልማት” የተሰኘ የ1 ቢሊየን ዶላር ኢኒቬቲቭ ይፋ አድርጋለች፡፡

ኢኒሼቲቩ በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማትን በማጠናከር በአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገትን እና ማህበራዊ ልማትን ለማሳለጥ እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ያለውን የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት ለማረጋጋት ከባሕረ ሰላጤው ቀጣና ሀገራት እና ሌሎች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ከሱዳን ጋር በተያዘያ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ፣ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት እና በመላ ሀገሪቱ ያልተገደበ የሰብዓዊ ተደራሽነት አስፈላጊነት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሁለቱም ወገኖች ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ዘላቂ ልማትን ለማሳደግ የታለሙ የጋራ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለመደገፍ በመካከላቸው ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

 

http://እየተጠናከረ የመጣው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ትብብር…

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.