Fana: At a Speed of Life!

አዳማ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ነው የተጠናቀቀው።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ስታዲያም ቀን 10 ሰዓት ላይ የተጀመረው የአርባ ምንጭ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ በፋሲል ከተማ 2 ለ 1 መሪነት የመጀመሪያውን አጋማሽ አጠናቅቀዋል።

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ባሕር ዳር ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ይገናኛሉ።

ቀደም ብሎ ቀን 7 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.