የሸበሌ ሪዞርት የዘመናዊ ሥነ ሕንጻ ጥበብ ከሶማሌ ክልል ባሕላዊ እሴት ጋር አቀናጅቶ የያዘ የታሪክ ማኅደር ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸበሌ ሪዞርት መዝናኛ ስፍራ ብቻ ሳይሆን የዘመናዊ ሥነ ሕንጻ ጥበብ ከሶማሌ ክልል ባሕላዊ እሴት ጋር አቀናጅቶ የያዘ የታሪክ ማኅደር ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ከ’ገበታ ለትውልድ’ ዐቢይ ፕሮጀክቶች መካከል ሁለተኛውን እና በ385 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውን የሸበሌ ሪዞርትን መርቀን ለአገልግሎት አብቅተናል ብለዋል።
ሪዞርቱ መዝናኛ ስፍራ ብቻ ሳይሆን የዘመናዊ ሥነ ሕንጻ ጥበብን ከሶማሌ ክልል ባሕላዊ እሴት ጋር አቀናጅቶ የያዘ የታሪክ ማኅደር መሆኑንም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጠ የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ትልቅ ሥራ ነው ሲሉም አመልክተዋል።
በክልሉ የሚገኘው እጅግ ሰፊ እና ማራኪ ተፈጥሯዊ ጸጋ በመደመር ዕሴትና ትብብር ወደ ልማት ሲለወጥ ኢትዮጵያ የምታልም ብቻ ሳትሆን ህልሟን ወደ እውነት የምትቀይር እና የምትኖር ሀገር መሆኗን በተግባር አሳይቷልም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Telegram https://fanamc.com/amharic/
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!