አርባምንጭ ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ18ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ ታምራት እያሱ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገውን ብቸኛ ግብ ፍሬው ሰለሞን ከመረብ አሳርፏል፡፡