Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ለውጡ ከመጣ ጀምሮ ኢትዮጵያ አንድም ዶላር በኮሜርሻል ብድር አልወሰደችም ይህም ከፍተኛ ምስጋና የሚገባው ጠንካራ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው።

👉 ያበደሩን ወዳጆቻችን ምንም እንኳን ብድሩ አራጣ ቢሆንም ተገቢ አይደለም እና ወደ ትክክለኛው የብድር ሥርዓት እንዲገባ የማድረግ ስራዎች ማከናወን ተችሏል።

👉 አሁን ላይ የኢትዮጵያ የብድር ሁኔታ መካከለኛ ወይንም የተሻለ የሚባል ይሆናል፤ ምክንያቱም ያለን የሀገር ውስጥ ምርት፣ ያለብን የዕዳ ጫና ወደዚያ ሊሄድ እንደሚችል የሚያመላክት ነው።

👉 አንድም ኮሜርሻል ብድር ሳንወስድ የነበረውን ስሁት የብድር ሥርዓት ለማሻሻል እና ለመቀየር ስንደራደር ስራዎቻችን ሰርተናል።

👉 በዚህም ሕዳሴን ካለ አንድ ብድር እና እርዳታ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚገኙ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም ጨክነው በጋራ በመቆም የተሳካ ፕሮጀክት ነው።

👉 በዚህ ሳያበቃ በአፍሪካ 3ኛ ደረጃ መያዝ የሚችል የኮይሻ ግድብም በስራ ላይ ነው።

👉 በተጨማሪም ከአፍሪካ 1ኛ የሆነው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ተጀምሯል።

👉 የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታም ኢትዮጵያ ውስጥ ተጀምሯል።

👉 የጋዝ ምርት የመጀመሪያ ዙር ጨርሰን ሁለተኛ ዙር እና የማጣሪያ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

👉 በሜጋ ፕሮጀክት በፕሮጀክት ክትትል፣ አፈጻጸም እና አመራር መላው አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ ይማራሉ።

👉 ቃል ገብተን ጀምረን እስካሁን ያልጨረስነው ፕሮጀክት እንደሌለ እና የስራ ባሕልም እያደገ መጥቷል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.