ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
👉 ባለፉት ዓመታት ከተከተልነው መንገድ ውስጥ የትምህርት ሥርዓቱን የማሻሻል ስራ አንዱ ነው።
👉 በዚህም የቅድመ መደበኛ ትምህርት ላይ አበክረን ሰርተናል።
👉 ዩኒቨርሲቲን በሚመለከት የነበሩንን ዩኒቨርሲቲዎች በተቻለ መጠን ጥራታቸው ላይ ለመስራት ጥረት አድርገናል።
👉 አሁን ባለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዓለም እውቀት ነጻ እና በሁሉም ቤት እኩል የሚደርስ ሆኗል።
👉 ብቃት ማለት የኮሌጅ ዲግሪ ሳይሆን ክህሎት ነው።
👉 የዛሬ መቶ ዓመት በነበረ አይነት አካሄድ ዘመኑን መዋጀት አይቻልም።
👉 እኛ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናስበው ያሉንን ዩኒቨርሲቲዎችን ጥራት ማሻሻል ነው።
👉 ታች ላይ በመስራትና የዲጂታል ክህሎትን በመገንባት ለነገ ውድድር መዘጋጀት ያስፈልጋል።
👉 የመምህራን ስልጠና፣ የመምህራን ኑሮ ማሻሻልና ቴክኖሎጂን መጠቀም ትምህርትን ይቀይራሉ።
👉 መምህራን ማወቅ ያለባቸው ሰው ከስልኩ የሚያገኘውን የዕውቀት ልክ የትኛውም ተቋም አይሰጠውም፥ ስለዚህ የቴክኖሎጂ ክህሎትን ማሳደግ ይገባል።
👉 የጸጥታ ችግር የዛሬን ትምህርት ማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን የተማሪዎችን ነገ ጭምር ነው የሚገድለው
👉 ልጆች ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ የሚከለክል ነጻ አውጪ ታጋይ ያልተማረ ሰው ሰብስቦ ነገ ምን አይነት መንግስት ይፈጥራል?
👉 ይሄ በጣም አደገኛ ስብራት ነው፥ ይሄንን መግራትና ማስተካከል ያስፈልጋል።
በዮናስ ጌትነት