ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።
ለጨረታ 70 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መቅረቡንና በሒደቱ 19 ባንኮች መሳተፋቸውን ጠቅሶ÷ 8 ባንኮች በጨረታው ማሸነፋቸውን ገልጿል።
በምንዛሪ ጨረታው አንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ በአማካኝ 155 ነጥብ 0506 ብር ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ቀድሞ በወጣው መርሐ ግብር መሰረት ተመሳሳይ ጨረታ በቀጣይ እንደሚያካሂድም አስታውቋል፡፡