ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለምንም ግብ ነው የተጠናቀቀው፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ እየተካሄደ ባለ ሌላኛ መርሃግብር መቻል እና ሀዲያ ሆሳዕና 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ እረፍት አምርተዋል፡፡