Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ምክር ቤት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 6ኛው የአፋር ክልል መንግሥት ምክር ቤት 5ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በሰመራ ከተማ እያካሄደ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት፣ የማኅበራዊና የኢኮኖሚ እንዲሁም የሰላምና ፀጥታ እንቅስቃሴዎችን ሪፖርት ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል።

በጉባኤው የቀረቡትን የሥራ ሪፖርቶችና የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማዎች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የምክር ቤቱ አባላት በቀረቡት ሰነዶች ላይ አስፈላጊውን ውይይትና ምክክር ካደረጉ በኋላ ሪፖርቶቹን እንደሚያጸድቁ ተመላክቷል።

ጉባኤው እስከ የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን÷ የምክር ቤቱ አባላት ሁለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይተው ያፀድቃሉ ተብሎም ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.