Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ምክር ቤት ከ657 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት 657 ሚሊየን 600 ሺህ ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል።

ትናንት የጀመረው የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ነው በዛሬው ዕለት የክልሉን ተጨማሪ በጀት ያጸደቀው።

በጀቱ በክልሉ ተጀምረው ላልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች እና አንገብጋቢ ለሆኑ አዳዲስ ፕሮጀክቶች የሚውል እንደሆነ ተመላክቷል።

ምክር ቤቱ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችንና አንድ ደንብ መርምሮ ከማጽደቅ በተጨማሪ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ እና የመንግሥት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መርምሮ ማጽደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ተቀብሎ አድቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.