በሁሉም ዘርፎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ ተግባራት ተከናውነዋል – አቶ አሻድሊ ሀሰን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በሁሉም ዘርፎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ ተግባራት ተከናውነዋል አሉ።
የክልሉ ምክር ቤት 6ኛው 5 ዓመት 2ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
የክልሉን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት አቶ አሻድሊ ሀሰን፤ ባለፉት ስድስት ወራት የክልሉን የማንሠራራት ዘመን ጅማሮ ያበሰሩ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
ክልሉ ከነበሩበት ችግሮች ወጥቶ ለሕዝብ የሚጠቅሙ እና ልማት የሚያፋጥኑ መሠረታዊ ምሰሶዎችን መገንባት መቻሉን ገልጸው፤ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን የተገኘው ስኬት ሰላም ሲኖር መሥራት እንደሚቻል አረጋግጠዋል ነው ያሉት።
ከልዩ አነስተኛ እና ባህላዊ ወርቅ አምራቾች 3 ሺህ 525 ኪ.ግ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት መታቀዱን ጠቅሰው፤ 4 ሺህ 158 ነጥብ 6 ኪ.ግ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ በማስገባት ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም 432 እምነበረድ ብሎክ፣ 2 ሺህ 532 የእምነበረድ ተረፈ ምርት እና 10 ሺህ 261 ሜትሪክ ኪዩብ እምነበረድ ቡልደር እንደተመረተ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
9 ሺህ 940 ቶን የድንጋይ ከሰል ምርት መገኘቱን አንስተው፤ ለ530 ልዩ አነስተኛ የወርቅ አምራቾች፣ ለ25 የድንጋይ ከሰል እና ለ33 የእምነበረድ አምራች ባለሃብቶች የምርት ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመዋል።