Fana: At a Speed of Life!

የቄጦ የመስኖ ፕሮጀክት የአካባቢውን የተፈጥሮ መልክዓ ምድር በአግባቡ ለመጠቀም የተተገበረ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቄጦ የመስኖ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት የአካባቢውን የተፈጥሮ መልክዓ ምድር በአግባቡ ለመጠቀም ታስቦበት የተተገበረ ነው አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ለሰዲ ጫንቃ እና ሃዋ ገላን ወረዳዎች ትርጉም ያለው ለውጥ እያመጣ ያለውን የቄጦ የመስኖ መሠረተ ልማት ፕሮጀክትን ለመመልከት እድል አግኝቻለሁ ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ለግብርና ሥራ የማይቋረጥ የውሃ አቅርቦትን በሚያረጋግጥ መልኩ የአካባቢውን የተፈጥሮ መልክዓ ምድር በአግባቡ ለመጠቀም ታስቦበት የተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል። ‎

የመስኖ ሥራውን በቀጥታ ጥቅም ላይ በማዋል የታረሰ እና የለማ መሬት ለሕብረተሰቡ ጉልህ ፋይዳ ማስገኘት መጀመሩም አበረታች እንደሆነ አመልክተዋል።

አብሮ የተሠራው የመንገድ መሠረተ ልማትም የገበያ ተደራሽነትን አስፍቷል፤ የነዋሪዎችን የቀን ተቀን ኑሮ እንቅስቃሴንም አቅልሏል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው።

አካባቢው እምቅ የግብርና አቅም ያለው እንደመሆኑ እንደ ስንዴ፣ ሩዝ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ እና ብርቱካን ያሉትን ምርቶች በመደገፍ ረገድ የመስኖ እና የመሠረተ ልማት ሥራ ዘላቂ የገጠር ግብርና ልማትን ማሳደግ እንደሚችሉ አብነት ነው ሲሉም አብራርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.