Fana: At a Speed of Life!

የሌላን ሀገር እጅ የማየት ምዕራፍ እየተዘጋ ነው – አቶ ሽመልስ አበዲሳ

‎አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቡሳ ጎኖፋ እየተሰሩ በሚገኙ ስራዎች የሌላን ሀገር እጅ የማየት ምዕራፍ እየተዘጋ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አበዲሳ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው ይህንን የገለጹት።

የመደመር እሳቤን መሰረት በማድረግ የሕዝቡን የጋራ እሴት እና የገዳ ሥርዓት ፍልስፍናን በማዋሄድ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከ20 ሺህ በላይ የቡኡራ ቦሩ ትምህርት ቤቶች፣ ከ660 በላይ የሕብረሰተብ ፋርማሲዎች እንዲሁም ከ7 ሺህ 300 በላይ የቀበሌ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች መገንባታቸውን አመልክተዋል።

የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠው÷ ፋብሪካው ሲጠናቀቅ የአርሶ አደሮችንና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል።

በክልሉ የሰፍትኔት ድጋፍ ሳይሆን በላቡ ሃብቱን አፍርቶ ለሌላው የሚተርፍ ዜጋ እየፈጠርን ነው ያሉት አቶ ሽመልስ÷ በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አንስተዋል።

በሲፈን መገርሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.