Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ እና በበርካታ መስኮች በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

በአዘርባጃን ባኩ ዛጉልባ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከተካሄደው ውይይት በመቀጠል ሁለቱ መሪዎች በመከላከያና በበርካታ መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነዶች የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

‎ከተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶች መካከል 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ32) ማዘጋጀት፣ በግብርና፣ በሚዲያ ልማትና ልምድ ልውውጥ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና በጸረ ሙስና ትብብር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው።

‎በሌላ በኩል የአዘርባጃንን የአገልግሎት ዘርፍ ዝመናን በግንባር ቀደምትነት እየመራ የሚገኘው ተቋም “አሳን” እና በኢትዮጵያ የመሶብ አገልግሎት መካከል በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

‎ስምምነቶቹ እና የመግባቢያ ሰነዶቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ እና እንደሚያስፋፉ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.