Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለዐድዋ ድል በዓል አከባበር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 130ኛው የዐድዋ ድል በዓል የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ይከበራል፡፡

ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቆ ወደ ሥራ መግባቱን የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥምና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በዚህ መሰረት:-

👉ከቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት፣

👉ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ፣

👉ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር፣

👉ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም፣

👉ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት፣

👉ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ ዳግማዊ ምኒለሰክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ኃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ፣

👉ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት ላይ ነገ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ፡፡

በተጠቀሱት ቦታዎች ለአጭርም ሆነ ለረዥም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ዜጎች ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሟቸው በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 ወይም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.