ማንቼስተር ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ያዘ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 2 ለ 1 በማሸነፍ የሶስተኛነት ደረጃን ከአስቶንቪላ ተረክቧል፡፡
11 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የማንቼስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ቤንጃሚን ሴሽኮ አስቆጥረዋል፡፡
ክሪስታል ፓላስን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ላክሮክስ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥቡን 51 በማድረስ ከአስቶንቪላ በግብ ክፍያ በልጦ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ብራይተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 1 እንዲሁም ፉልሃም ቶተንሃም ሆትስፐርን 2 ለ1 አሸንፈዋል፡፡