Fana: At a Speed of Life!

ነገ በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው ኢፍጣር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የኢፍጣር መርሐ ግብር ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይደረጋሉ አለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ።

በዚህም መሰረት፡-

👉ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን፣

👉ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ፣

👉 ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፣ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ፣

👉 ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ፣

👉 ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ፣

👉ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ፣

👉ከአዋሬ አካባቢ በካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንቲኔታል አካባቢ ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጣር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ።

በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ዜጎች ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሟቸው በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.