Fana: At a Speed of Life!

የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፕሮግራም ተጠናቅቆ መንገዱ ለተሽከርካሪዎች ክፍት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፕሮግራም ተጠናቅቆ መንገዱ ለተሽከርካሪዎች ክፍት ተደርጓል አለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፡፡

1447ኛውን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ትብብር «ነጃሺ ለሀገር» በሚል መሪ ሐሳብ ለ6ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳየች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ ሀገራት እንግዶች እና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በሰላም መጠናቀቁን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

ፕሮግራሙ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምስጋና አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.