የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በአሁኑ ትውልድ ይመለሳል – ጄኔራል ይመር መኮንን
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በአሁኑ ትውልድ ይመለሳል አሉ በመከላከያ ሰራዊት የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ይመር መኮንን፡፡
ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሰራዊት ማሕበር ትኩረቱን ቀይ ባሕር ላይ ያደረገ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
ጄኔራል ይመር በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያና ቀይ ባሕር ጥልቅ ተፈጥሯዊ ትስስር ያላቸው የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፡፡
በታሪክ የውጭ ወረራ መከላከያ ጋሻ፣ መገናኛ እና የንግድ መስመራችን ነበር ያሉት ጄኔራሉ÷ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ያላት ተሳትፎና የሚኖራት ተደራሽነት መረጋገጥ ብሔራዊ ጥቅሟንና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የላቀ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ያነሳችው የሕልውና ጥያቄ ግጭት የሚቀሰቅስ ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነትና ቀጣናዊ ትስስር ለማረጋገጥ የሚደረግ ጥረትና የሰጥቶ መቀበል መርህን ያስቀደመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በሻገር ቀጣናውን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር የቀጣናውን ሕዝቦች አንድነት እንደሚያጠናክርም ጠቁመዋል፡፡
የቀይ ባሕር ጉዳይ የሕልውና ጉዳይ እንደመሆኑ በሀገሪቱ የሚገኙ ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሰራዊት ማሕበር አባላት ሊገነዘቡ ይገባልም ነው ያሉት።
በመራኦል ከድር