Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ባለፉት 60 ዓመታት በሰራችው ሥራ ከ87 በላይ የጥበቃ ቦታዎች ባለቤት ሆናለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ባለፉት 60 ዓመታት በሰራችው ሥራ ከ87 በላይ የጥበቃ ቦታዎች ባለቤት ሆናለች አለ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን፡፡

‘60 ዓመታት ለኢትዮጵያ የዱር ሕይወት’ በሚል መሪ ሀሳብ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን 60ኛ ዓመት በዓል የማብሰሪያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ በወቅቱ እንዳሉት፤ ተቋሙ ባለፉት ዓመታት በሰራው ሥራ በተፈጥሮ ጥበቃ መስክ ስኬት አስመዝግቧል፡፡

የዱር ሕይወት ጥበቃ ላይ የተሳተፉ ሬንጀሮች እና የየአካባቢዎቹ ማህበረሰብ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ በቀለ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብርቅዬ እንስሳት የብሔራዊ ማንነታችን አካል ናቸው ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ሥራዎች ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት ብዝሀነት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች ነው ያሉት።

ሕገ ወጥ አደን፣ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ፣ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ እና ፋይናንስ ለዘርፉ ተግዳሮቶች መሆናቸው ጠቅሰው፤ ተግዳሮቶችን መፍታት የአንድ ጊዜ ሥራ ብቻ ሳይሆን ሂደት የሚፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዚህም ሁሉም ባለድርሻዎች በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.