Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በቴል አቪቭ ከ100 በላይ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ፈጸመች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢራን በእስራኤል ላይ በወሰደችው የአፀፋ ምላሽ በቴል አቪቭ ከ100 በላይ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች፡፡

የኢራን አብዮታዊ ዘብ እንዳስታወቀው÷ ጥቃቱ በትናንትናው ዕለት በእስራኤል ጥቃት ለተገደሉት ራስ ገዝ የደኅንነት መሪ አሊ ላርጃኒ የተሰጠ አፀፋ ነው፡፡

በአፀፋ ጥቃቱ ኮሮማሻር-4፣ ቃድር፣ ኤማድ እና ኬባር ሼካን ሚሳኤሎች ጥቅም ላይ መዋላቸው ተገልጿል፡፡

አብዮታዊ ዘቡ ከቴል አቪቭ በተጨማሪ በሀይፋ ወደብ፣ ኢየሩሳሌም እና ቤርሳቤህ ከተሞች በሚገኙ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙንም አስታውቋል፡፡

በትናንት ምሽቱ ጥቃት ብቻ 192 ሰዎች ሲጎዱ 11 ሰዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የእስራኤል ጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡

በሌላ በኩል እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ እያካሄደች ባለው የምድር ላይ ዘመቻ በዛሬው ዕለት በመካከለኛው ቤሩት መጠነ ሰፊ ጥቃት ሰንዝራለች፡፡

በዚህ የእስራኤል የምድር ላይ ዘመቻ የሟቾች ቁጥር 912 መድረሱን አልጃዚራ ዘግቧል፡፡

19ኛ ቀኑን በያዘው በዚህ ጦርነት አሜሪካ በሆርሙዝ ሰርጥ ሰርሳሪ ቦምቦችን በመጠቀም በኢራን የሚሳኤል ስፍራዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ቢቢሲ፣ ፕሬስ ቲቪ እና አልጃዚራ ዘግበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.