በመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት የተነሳ የዓለም ገበያ ስጋት በአጭሩ፡-
🫵አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ከ$116 በላይ እየተሸጠ ነው፣
🫵ጋዝ በአውሮፓ ገበያ ከ 30% በላይ ጭማሪ አሳይቷል፤
🫵ግጭቱ ካልቆመና የኢነርጂ አቅርቦት ካልተስተካከለ የንግድ እድገት በ1.4% እንደሚቀንስ ዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት እያሳሰበ ነው፤
🫵በሆርሙዝ እና በባበል መንደብ መርከቦች ለማለፍ እየተቸገሩ ይገኛሉ፤
🫵የጭነት ዋጋ እና የኢንሹራንስ ጉዳይም አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል፤
🫵አውስትራሊያ ግጭቱ ቶሎ መቋጫ ካላገኘ ዓመታዊ እድገቷ በ0.6% እንደሚቀንስ፤ የዋጋ ንረት 5% ሊደርስ እንደሚችል ስጋቷን ገልጻለች፤
🫵ማሌዢያ ጉዳዩ የኢነርጂ ፍጆታ ወጪዋን ሊያንር እንደሚችል እየወተወተች ትገኛለች፡፡
በመሆኑም በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሳ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገራት እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል።
የአቅርቦት ሥርዓቱ ወደ መደበኛው እስኪመለስ ድረስም አማራጮችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡-
• ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም፣
• አጫጭር መንገዶችን በእግር በመጓዝ፣
• ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት በመጠቀም፣
• ብስክሌት በመጠቀም፣
• የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም፣
• ለረዥም ርቀት ከግል ይልቅ የህዝብ ትራንስፖርት በመጠቀም፣
• ወደ ተመሳሳይ አቅጣጫ የሚደረግ ጉዞን ከወዳጅ ጋር በማቀናጀት፣
• በኦንላይን በመስራት ነዳጅን በቁጠባ እና ወጪ በቀነሰ መንገድ ለመጠቀም እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ስለዚህ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት በሃላፊነት ስሜት እንዲጠቀሙ ይመከራል፡፡