ሀዋሳና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲዎች በጤና ዘርፍ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀዋሳ እና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲዎች በጤና ዘርፍ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሕክምና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 427 ተማሪዎች ነው ያስመረቀው፡፡
በዚህ መሰረትም በሕክምና ዶክተሬት 88 ፣ በጤና ሳይንስ በመጀመሪያ ዲግሪ 268 ፣ በስፔሻሊቲ 70 ተማሪዎች እንዲሁም በሰብ ስፔሻሊቲ 1 ተማሪ መመረቃቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ እንዲሁም በስፔሻሊቲ ያሰለጠናቸውን 616 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ 478 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 128 በ2ኛ ዲግሪ ፣ 3 በዶክትሬት ዲግሪ እንዲሁም 7 በእስፔሻሊቲ የሰለጠኑ ናቸው፡፡
በተመስገን ቡልቡሎ እና ነጌሶ ከድር