‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለእኛ ከሐውልት በላይ ነው – አቶ አወል አርባ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለእኛ ከሐውልት በላይ ነው፤ ለሕዝቡ ትርፍ ያለውና የሚጠቀምበት ነው አሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት የ’ገበታ ለትውልድ’ ውጥን አካል የሆነውን ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ አስመርቀዋል።
አቶ አወል በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፕሮጀክቱን ለመጠበቅ፣ ለማቆየትና ቱሪስት በመሳብ የጎሳ አካል ማድረግ ከሁሉም አፋር የሚጠበቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዜጎች ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ እንዲጎብኙ ጥሪ ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የሎጅ ግንባታው እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በአድማሱ አራጋው