Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ዘመኑን የዋጀና ቀልጣፍ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በማስፋት አገልግሎት አሰጣጥን እያሻሻለ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባ አዳነች በመዲናዋ ሶስተኛ የሆነውን አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ልደታ ቅርንጫፍ በዛሬው ዕለት ሥራ አስጀምረዋል።

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ቅሬታዎችን ለመመለስ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው፡፡

አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዲጂታል የታገዘ አሰራርን በማጠናከር የማሕበረሰቡን እርካታ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስጀመር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡

በመዲናዋ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ሥራ ከገባ ወዲህ 120 ሺህ ዜጎች አገልግሎት ማግኘታቸውን ነው የገለጹት፡፡

በዛሬው ዕለት ሥራ የጀመረው አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 20 ተቋማትን እና 112 አገልሎቶችን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.