Fana: At a Speed of Life!

ዜጎች ለኑሮ ከተማ ከሚቀይሩ የአኗኗር ባህላቸውን ቢያሻሽሉ ይመረጣል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዜጎች ለኑሮ ከተማ ከሚቀይሩ የአኗኗር ባህላቸውን ቢያሻሽሉ ይመረጣል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ከተማ፣ ከተሜነት፣ ክትመት እና የኮሪደር ልማት በሚል መሪ ሐሳብ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም በማህበራዊ ዘርፍ ከተቀመጠው ግብ አንጻር የኑሮ ደረጃን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሥራዎችን ሰርተናል ብለዋል፡፡

ከተደራሽነት አንጻር አንድ ሰው የሚፈልገውን ነገር በሚያውቀው ርቀትና በሚገምተው ሰዓት የማግኘት አቅሙን ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ይህ እቅድ በትምህርት ቤት፣ በጤና፣ በሱፐር ማርኬት፣ በገበያ አዳራሽ እና በሁሉም አገልግሎት ዘርፎች እያደገ መሄድ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ በየሰፈሩ ፓርኮችን ስለገነባን አንድ መከካከለኛ ገቢ ያለው ቤተሰብ ባለበት አካባቢ መዝናናት እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማዜጎች ለኑሮ ከተማ ከሚቀይሩ የአኗኗር ባህላቸውን ቢያሻሽሉ ይመረጣል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዜጎች ለኑሮ ከተማ ከሚቀይሩ የአኗኗር ባህላቸውን ቢያሻሽሉ ይመረጣል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ከተማ፣ ከተሜነት፣ ክትመት እና የኮሪደር ልማት በሚል መሪ ሐሳብ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸውም በማህበራዊ ዘርፍ ከተቀመጠው ግብ አንጻር የኑሮ ደረጃን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሥራዎችን ሰርተናል ብለዋል፡፡

ከተደራሽነት አንጻር አንድ ሰው የሚፈልገውን ነገር በሚያውቀው ርቀትና በሚገምተው ሰዓት የማግኘት አቅሙን ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ይህ እቅድ በትምህርት ቤት፣ በጤና፣ በሱፐር ማርኬት፣ በገበያ አዳራሽ እና በሁሉም አገልግሎት ዘርፎች እያደገ መሄድ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ በየሰፈሩ ፓርኮችን ስለገነባን አንድ መከካከለኛ ገቢ ያለው ቤተሰብ ባለበት አካባቢ መዝናናት እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ላይ ብቻ ከ1 ሺህ 600 በላይ የእግር ኳስ መጫወቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባቱን ጠቅሰው ÷በዚህም ከስራ መልስ ሰዎች እግርኳስ ሲጫወቱ ማየት እየተለመደ መጥቷል ብለዋል፡፡

የመዝናኛ ስፍራዎቹ በቂ ላይሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እስካሁን የተገነቡት ለነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባን ውበት ሰው በቀላሉ አይቶ መረዳት ይችላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ጨለማ ሁሌም ያስፈራል፤ ለዚያም ነው ሁሉም አካባቢ ብርሃን እንዲሆን የተደረገው ብለዋል፡፡

በየአካባቢው የተተከሉ መብራቶች ከውበት በተጨማሪ የሰፈር ሰላምና ደህንነት እየጠበቁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በአጠቃላይ ሰዎች ኮሪደርን ለመተቸት ከመሞከራቸው በፊት የተከናወኑ ተግባራትን እና የተሳኩ ግቦችን መመልከት አለባቸው ነው ያሉት፡፡

በርካታ ሀገራት የከተማ መጨናነቅን ለመቀነስ ብዙ ርቅት ተጉዘው ሌላ ዋና ከተማ መፍጠራቸውን ገልጸው÷ እኛ ግን ያንን አላደረግንም ከተማ ከመቀየር የአኗኗር ባህል መቀየር ይሻላል ብለዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ ላይ ብቻ ከ1 ሺህ 600 በላይ የእግር ኳስ መጫወቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባቱን ጠቅሰው ÷በዚህም ከስራ መልስ ሰዎች እግርኳስ ሲጫወቱ ማየት እየተለመደ መጥቷል ብለዋል፡፡

የመዝናኛ ስፍራዎቹ በቂ ላይሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እስካሁን የተገነቡት ለነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረቡ መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባን ውበት ሰው በቀላሉ አይቶ መረዳት ይችላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ጨለማ ሁሌም ያስፈራል፤ ለዚያም ነው ሁሉም አካባቢ ብርሃን እንዲሆን የተደረገው ብለዋል፡፡

በየአካባቢው የተተከሉ መብራቶች ከውበት በተጨማሪ የሰፈር ሰላምና ደህንነት እየጠበቁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በአጠቃላይ ሰዎች ኮሪደርን ለመተቸት ከመሞከራቸው በፊት የተከናወኑ ተግባራትን እና የተሳኩ ግቦችን መመልከት አለባቸው ነው ያሉት፡፡

በርካታ ሀገራት የከተማ መጨናነቅን ለመቀነስ ብዙ ርቅት ተጉዘው ሌላ ዋና ከተማ መፍጠራቸውን ገልጸው÷ እኛ ግን ያንን አላደረግንም ከተማ ከመቀየር የአኗኗር ባህል መቀየር ይሻላል ብለዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.