የኢትዮጵያ የዲጂታል ምህዳር ጉዞ በዓለም የዲጂታል ዘርፍ እድገት ተወዳዳሪ እየሆነ ነው – አቶ ሃይሉ አዱኛ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የዲጂታል ምህዳር ጉዞ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ዘርፍ እድገት ተወዳዳሪ እየሆነ መጥቷል አሉ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ።
የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት ፎረም የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን አመራሮች እና የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
አቶ ሃይሉ አዱኛ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በመንግሥትና ሕዝብ መካከል መልካም ግንኙነትና መተማመንን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡
የወል ትርክት እና መልካም ገጽታን ለመገንባት እንዲሁም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመመከት የመገናኛ ብዙሃን ቅንጅት አስፋላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ተቋማቸው በሁሉም ዘርፍ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት መረጃን ዲጂታላይዝ ከማድረግ ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የዲጂታል ሥርዓቱ አሁን ካሉ የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች መረጃን ከመሰብሰብ ባለፈ ከመገናኛ ብዙሃን፣ ከመንግሥት ተቋማትና ከሕዝቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያስችላል ነው ያሉት፡፡