Fana: At a Speed of Life!

የሹዋሊድ በዓል በሀረር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም የሳይንስ የትምህርትና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የሹዋሊድ በዓል በሀረር ከተማ እየተከበረ ነው።

በሀረሪ ብሔረሰብ ዘንድ የኢድ አልፈጥር በዓል ከተከበረ ከስድስት ቀናት በኋላ የሚከበረው የሹዋሊድ በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ይገኛል።

የዘንድሮ በዓል “ሹዋሊድ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን እና ለቱሪዝም እድገታችን” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የሚከበረው።

በበዓሉ በሀረር ከተማ የባህል፣ ፌስቲቫል እና አውደ ርዕይ፣ የልማት ስራዎች ጉብኝትን ጨምሮ ሌሎች መርሐ ግብሮች ይከናወናሉ።

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.