Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኮተቤ 02 ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

18 ሰዎችን ጭኖ ከአንቆርጫ ወደ ላምበረት በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ዛሬ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ከ30 በደረሰ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አሽከርካሪውን ጨምሮ በ16 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች የህክምና ርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑ ፖሊስ ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.