በኢራን የድሮን ጥቃት የደረሰበት የአል ሳልሚ የድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ…
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢራን የድሮን ጥቃት የደረሰበት የአል ሳልሚ የድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከባድ ጉዳት ሳይደርስበት አደጋው በቁጥጥር ስር መዋሉን የኩዌት መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡
የኩዌት ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው ጥቃቱን ተከትሎ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ምንም አይነት ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የገለጸው፡፡
የኩዌት ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ አል ሳልሚ አደጋው የደረሰበት ከዱባይ ወደብ ወጣ ብሎ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የባህር ዳርቻ ላይ በሚገኝበት ወቅት ነው፡፡
በአደጋው በአካባቢው የባህር ውሃ እና ነዳጅ ላይ የደረሰ ብክለት አለመኖሩም ተጠቁሟል፡፡
24 የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ላይ አደጋውን ተከትሎ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱ የተገለጸ ሲሆን ሌሎች የደረሱ ጉዳቶች አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ ተጨማሪ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከመንግስት ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ጋር በተጨማሪ ርምጃዎች ዙሪያ በትብብር እንደሚሰራ ይፋ ማድረጉን ገልፍ ታይምስ ዘግቧል፡፡
በአቤል ነዋይ