Fana: At a Speed of Life!

የገጠሩን የኢትዮጵያ ክፍል የአማራጭ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገጠሩን የኢትዮጵያ ክፍል የአማራጭ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ሰላማጎ ወረዳ ከ600 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የገሮ እና ወይደይ የሶላር ሚኒግሪድ ኃይል ማመንጫዎች ተመርቀዋል።

የገሮ ሶላር ኃይል ማመንጫ 625 ኪሎዋት የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፥ ወደ 6 ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው የተገለጸው፡፡

ሌላኛው በዞኑ የተመረቀው የወይደይ ሶላር ሚኒግሪድ ፕሮጀክት ደግሞ 200 ኪሎዋት በማመንጨት 2 ሺህ አባወራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተመላክቷል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሱልጣን ዎሊ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የገጠሩን የኢትዮጵያ ክፍል የአማራጭ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም ከነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ወደ ተቋማት የታዳሽ ኃይል ተጠቃሚነት እየተሸጋገረ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማስፋት መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.