የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት በቡድን ያደራጇቸውን አጀንዳዎች አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት በቡድን ያደራጇቸውን አጀንዳዎች ለዋናው መድረክ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰብ በትናንትናው ዕለት በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረኩ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን፥ የትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት በቡድን ያደራጇቸውን አጀንዳዎች ለዋናው መድረክ አቅርበዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የማኅበራትና ተቋማት እንዲሁም የታዋቂ ግለሰቦች ቡድኖች አጀንዳዎቻቸውን ካቀረቡት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።
ኮሚሽኑ የቀረቡትን የቡድን አጀንዳዎች ከሁሉም ቡድኖች በተመረጡ አደራጅ ኮሚቴ በአንድ ከተደራጁ በኋላ በነገው ዕለት እንደሚረከብ ገልጿል ።