Fana: At a Speed of Life!

ተጠናክሮ የቀጠለው የኢትዮጵያ እና ቻይና አጋርነት…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና በኢትዮጵያ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት አሉ የሀገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚያኦ ዴዩ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
አቶ አህመድ ሺዴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የኢትዮጵያ እና ቻይና አጋርነት በ2024ቱ የቻይና አፍሪካ ስምምነት (ፎካክ) መሰረት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በአፍሪካ፣ ቻይና እና በዓለም ገበያ መካከል ያለውን ግንኙነት ያሳድጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ ቁልፍ ሀገራዊ የመሠረተ ልማት ውጥኖችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ሚያኦ ዴዩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጭነት ያሰመዘገበችውን የኢኮኖሚ እድገት አድንቀው፥ ሀገራቸው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡
በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድ የሚኖራትን ሚና በተመለከተ ምክክር አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበርና በጋራ የልማት ግቦች ላይ የተመሰረተ የደቡብ ለደቡብ ትብብር ተምሳሌት ሆኖ እንደሚቀጥል መገለጹን የገንዘብ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.