አሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ ከጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ ከጣሊያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል፡፡
አሰልጣኙ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን ወደ 2026 ዓለም ዋንጫ ማሳለፍ ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው ለቅቀዋል፡፡
ጣሊያን ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ከዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኗ ይታወቃል፡፡
አሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን በ2025 የተረከቡ ሲሆን÷ 8 ጨዋታዎችን በማድረግ 6 ድል፣ 1 አቻ እና 1 ሽንፈት አስመዝግበዋል፡፡
ጅናሮ ጋቱሶ ጣሊያን ለመጨረሻ ጊዜ በፈረንጆቹ 2006 የዓለም ዋንጫን ስታሳካ በተጫዋችነት የስብስቡ አካል እንደነበር ይታወሳል፡፡
በትናንትናው ዕለት የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጋብሪኤል ግራቪና እና የብሔራዊ ቡድኑ መሪ ጂያንሉጂ ቡፎን ከኃላፊነት መልቀቃቸው አይዘነጋም፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ