Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ለሀገራዊ ለውጡ ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች በለውጡ ለተገኘው ድልና ስኬት እውቅና የሚሰጥ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በድጋፍ ሰልፉ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች የለውጡን መንግሥት ጉዞ የሚደግፉና የቀጣይነቱን አስፈላጊነት የሚያንጸባርቁ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተጋብተዋል፡፡

በዚህም ከመጋቢት እስከ መጋቢት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን ÷ በመጋቢት 24 ተምሳሌታዊ ጉዞ እና መሰረታዊ ርምጃ የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል።

በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ በቀጣይም የተሻለ ሥራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም መጋቢት 24 ጠንካራ መሰረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሰረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው እና የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልፅግና ነው የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.