Fana: At a Speed of Life!

በሐረር በለውጡ መንግሥት ለመጣው ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረር ከተማ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት በማስመልከት ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

”ከመጋቢት እስከ መጋቢት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

ሰልፈኞቹ ከሀገራዊ ለውጥ ወዲህ የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚያወሱና የተገኙ ድሎችን ለማስቀጠል ያላቸውን ዝግጁነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ በመጋቢት ብርሃን ወደ ዓለም አቀፍ ልዕልና፣ የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልፅግና ነው፣ አዲሲቷን ሐረር በታመነ ቃልና በተለወጠ ባህል እንገነባለን የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡

በተስፋዬ ሃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.