Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካና ኢራን የ45 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ እና ኢራን ተደራዳሪ ልዑካን የ45 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እየመከሩ ነው፡፡

በድርድሩ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀዲ ቫንስ፣ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ እና የፓኪስታን ጦር አዛዥ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ተሳትፈዋል፡፡

ድርድሩ የ45 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከመድረስ ባለፈ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይሁን እንጂ የተኩስ አቁም ውይይቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካስቀመጡት ቀነ ገደብ አስቀድሞ ሊጠናቀቅ የሚችልበት እድል ጠባብ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በድርድር መድረኩ አሜሪካ በሲቪል የሃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም እንዲሁም ኢራን በገልፍ ባህረ ሰላጤው ነዳጅና የውሃ ማጣሪያዎች ላይ ልትወስድ ያሰበችውን አጸፋ ለማስቆም ወሳኝ ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ውይይቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድትከፍት ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ ዛሬ ምሽት የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ትራምፕ ለአክሲዮስ የዜና ወኪል በሰጡት አስተያየት “ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የሚደረስበት ምርጥ እድል አለ ፤ በቀረቡ የተኩስ አቁም ሃሳቦች ኢራን የማትስማማ ከሆነ ግን ትፈራርሳለች” ሲሉ ዝተዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.