ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ መሳይ ሰለሞን ባለቀ ሰዓት ባስቆጠረው ግብ ወላይታ ድቻ ማሸነፍ ችሏል።
ቀደም ብሎ በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ሀድያ ሆሳዕና አርባ ምንጭ ከተማን 1 ለ 0 እንዲሁም ፋሲል ከነማ ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ÷ ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡