Fana: At a Speed of Life!

መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም አለሙ እና ዓብዱለጡፍ ባምባ አስቆጥረዋል፡፡

የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዳዊት ገብሩ ከመረብ አሳርፏል።

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አርባ ምንጭ ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 10 ሰዓት ላይ ያገናኘው ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 1 መሪነት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቅቋል።

እንዲሁም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ እና ምድረ ገነት ሽረ በተመሳሳይ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ቀደም ብሎ በተደረገ የሊጉ መርሐ ግብር ጨዋታ ሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ 1 ለ 1 አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.