Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች ተሰጥቷል አለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፡፡

የአገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት ÷ ተቋሙ በመደበኛና አስቸኳይ ፓስፖርት፣ የቪዛ እና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ አገልግሎቶችን ለደንበኞች እየሰጠ ነው፡፡

በተጨማሪም በአየር እና የብስ ድንበር ቁጥጥር እና ሌሎች አገልግሎቶች ላይ ስኬታማ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባለፋት ዘጠኝ ወራት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች መስጠት እንደተቻለ መጥቀሳቸውንም የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አምቦ መቃሳ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል 824 ሺህ 951 ቪዛ እና 29 ሺህ በላይ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ መሰጠቱን አስረድተዋል፡፡

በአየር እና በየብስ ድንበር ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ በጉዞ ሰነድ ከ5 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት ተሰጥቷል ነው ያሉት፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ አስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ፣ በሕገ ወጥ ደላላዎችና የተቋሙን ስም በአሉታዊ መንገድ እንዲነሳ ያደረጉ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.