Fana: At a Speed of Life!

ሊቨርፑል ከፒኤስጂ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ይጀምራሉ፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በፓርክ ደ ፕሪንስ ያደረጉትን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ፒኤስጂ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት በሜዳው በሚያደርገው ጨዋታ ውጤቱን ቀልብሶ ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአምና የመድረኩ አሸናፊ ፒኤስጂ በበኩሉ ውጤቱን አስጠብቆ ቀጣዩን ዙር ለመቀላቀል የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡

በ2024/25 የውድድር ዓመት በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ተገናኝተው ፒኤስጂ ሊቨርፑልን ከውድድሩ ውጪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ፒኤስጂ ሦስቱን ሲያሸንፍ ሊቨርፑል በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የመጀመሪያውን ዙር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ባርሴሎና ሦስቱን ሲያሸንፍ አትሌቲኮ ማድሪድ በሁለቱ ድል አድርጓል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.