ለአፍሪካ ሀገራት አርዓያ የሚሆነው የኢትዮጵያ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ …
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ለአፍሪካ ሀገራት አርአያ የሚሆን ነው አሉ የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ፡፡
በላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የተመራ ልዑክ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጎብኝት አድርጓል፡፡
ሚኒስትሯ ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ያለው አገልግሎት አሰጣጥ በከፍተኛ ደረጃ ዘምኗል።
በአገልግሎት ዘርፍ ለአፍሪካ አርአያ መሆን የሚችል ስራ ኢትዮጵያ ማከናወኗን መመልከታቸውን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በቴክኖሎጂ እና በመንግስት አገልግሎት በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ጉብኝቱ ለአፍሪካ ሀገራት ልምድ የማካፈል ጅማሮ አካል መሆኑን የፌደራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮናስ አለማየሁ አስረድተዋል።
በክብረወሰን ኑሩ