ትኩረት ከተሰጣቸው ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራ ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንደ ሀገር ትኩረት ሰጥተን እየሰራንባቸው ከሚገኙት ምርቶች አንዱ የሆነው የበቆሎ መስኖ ሥራችን ከፍ ባለ ስኬት ላይ ይገኛል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ በትኩረት እየተከናወነ የሚገኘው የበቆሎ መስኖ ሥራ ከፍተኛ ስኬት ላይ እንደሚገኝ አውስተዋል፡፡
የተገኘው ጅምር ውጤት ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ከመቀበል ወጥታ እራሷን መመገብ የምትችል ሀገር የማድረግ ታላቁ ሕልማችን እውን የሚሆንበት መንገድ ላይ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል።