የሊጉን መሪነት ለመረከብ ከበርንሌይ የሚጫወተው ማንቼስተር ሲቲ …
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በርንሌይ በሜዳው ተርፍ ሙር ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሚካሄደው ጨዋታ በርንሌ የሚሸነፍ ከሆነ በይፋ ከሊጉ መውረዱን ያረጋግጣል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በበኩሉ ጨዋታውን በድል ማጠናቀቅ ከቻለ የፕሪሚየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ከአርሰናል በመረከብ መምራት ይጀምራል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የአማካዩን ሮድሪ ግልጋሎት በጉዳት ምክንያት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ አረጋግጠዋል፡፡
በሌላ ጨዋታ ቦርንማውዝ ከሊድስ ዩናይትድ በተመሳሳይ 4 ሰዓት ይገናኛሉ።